Latest / SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

"የዛጉዌ መንግሥት ዋነኛው የውድቀት ምንጭ የስልጣን ወራሾች ያደረሱት የእርስ በእርስ ቀውስ ነው" ዶ/ር ደረሰ አየናቸው
ዶ/ር ደረሰ አየናቸው፤ የቀድሞው የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ድኅረ ምረቃ ዲን፣ የታሪክ ተባባሪ ፕሮፌሰርና በኤይክስ ማርሴል ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛ ዘመን የአፍሪካ ቀንድ ጥናትና ምርምር ፕሮግራም ተመራማሪ ናቸው። ሰሞኑን በፀሐይ አሳታሚ ድርጅት አማካይነት ባበቁት "ታሪከ ነገሥት ዘኢትዮጵያ፤ ከንጉሥ ዘርአ ያዕቆብ እስከ ንጉሥ ናኦድ (1426-500) መፅሐፋቸው ውስጥ ተካትተው ያሉትን የንጉሥ እስክንድር፣ አምደ ፅዮንና ናኦድ ዘመነ መንግሥታት አንስተው ይናገራሉ።
The skinny
The skinny isn't ready yet — notes appear once the transcript is processed.