Latest / SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

"ሀገራችንን በእናት የምንመስላት በጣም ስለምንወዳት ነው፤ እናት የፍቅር ተምሳሌት ናት" ሜሮን ተስፋዬ
ወ/ት ሰላማዊት ወሰን ከብሪስበን "በተለይ ያለ አባት ልጆቻቸውን ላሳደጉ እናቶች 'እንኳን ለእናቶች ቀን አደርሳችሁ' ማለት እፈልጋለሁ" ሲሉ፤ ወ/ሮ ቤተልሔም ጥበቡ ከሜልበርን "እናትነትን በቃላት መግለፅ አይቻልም፤ እናትነት ትልቅ ስጦታ ነው" ይላሉ፤ ወ/ሮ ሜሮን ተስፋዬም "የእናቶችን ቀን ማሰብ የሚገባን በየዕለቱ ነው" በማለት የእናቶችና የእናት ተምሳሌዎችን የክብር መዘከሪያና ሞገስ ማላበሻዋን "የእናቶች ቀን" አስመልክተው የእናትና ልጅ ግለ ሕይወታቸውን አጣቅሰው ያጋራሉ። አቶ ኢዮብ ቀፀላም ከሲድኒ፤ ሀገር ቤት ለሚገኙት ውድ እናታቸው የእናቶች ቀን መልካም ምኞታቸውን ያስተላልፋሉ።
The skinny
The skinny isn't ready yet — notes appear once the transcript is processed.