Shows / SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Episodes
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛበወሲባዊ ጥቃት ጥርጣሬ ሳቢያ በአምስት የሲድኒ ስዋንስ እግር ኳስ ተጫዋቾች ላይ ግደባ ተጣለ
በመጪው የፀደይ ወራት በመላ አውስትራሊያ የደን ቃጠሎ ሊጨምር እንደሚችል ተመለከተ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛአዲሱ የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት በ15 ሀገሮች በሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ለኢትዮጵያውያን ዜጎች መሰጠት መጀመሩን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ገለጠ
በኢትዮጵያ 4 በመቶ የሚሆኑ ወንዶች በጡት ካንሰር ይጠቃሉ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"ለበዓለ ደብረ ታቦር እንኳን አደረሳችሁ፤ አደረሰን!" መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረ ሥላሴ ጎበና
መልአከ ፀሐይ ቆሞስ አባ ገብረ ሥላሴ ጎበና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የሰሜን አፍሪካ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ ስለ በዓለ ደብረ ታቦር በሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ኦማን ለዩናይትድ ስቴትስና ኢራን የሰላም ስምምነት ደንቃራ ከሆነች በአሜሪካ ቦምብ ልትጋይ እንደምትችል አስጠነቀቁ
የኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ የጤና ሠራተኞች በከፍተኛ ፍጥነት እየተዛመተ ያለውን የኢቦላ ወረርሽኝ ለመቋቋም ብርቱ ፈተና ገጥሟቸው እንዳለ ተመለከተ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ‘በርካታ ሠራተኞች የጡረታ አበል ተቀማጫቸውን አስቀድመው ለቤት ብድርና ኑሮ መደጎሚያ ቢያውሉት የተሻለ ሁኔታ ላይ ይሆናሉ’ የሚለው የዋን ኔሽን ዕሳቤ ተቃውሞና ድጋፍ ገጥሞታል
ሩብ ሚሊዮን ያህል አውስትራሊያውያን የምግብና ግሮሰሪ አድራሾች ለመጀመሪያ ጊዜ በሰዓት ታሳቢ ክፍያ ሊያገኙ ነው
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦቻቸውን ብቻ ሳይሆን አውስትራሊያውያን ወዳጆቻቸውንም ጨምረው በአዲሱ ዓመት ዝግጅታችን ላይ እንዲገኙ እንጋብዛለን" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው ፤ በቪክቶሪያ ኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት፤ ቅዳሜ ሴፕቴምበር 5 / ነሐሴ 30 በፉትስክሬይ ፓርክ ከ11: 00 am እስከ 5:00 pm ስለሚከበረው የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት 2019 ቅበላ መሰናዶን አስመልክተው ይናገራሉ።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛበኢትዮጵያ የሚገነባው የቢሾፍቱ ሜጋ አውሮፕላን ማረፊያ በቻይናና አሜሪካ ኩባንያዎች መካከል ከፍተኛ ጂኦፖለቲካዊና የንግድ ፉክክር ማዕከል ሆኗል ተባለ
የሴት የመስተንግዶ ሠራተኞችን አለባበስና ጌጣጌጥ የሚወስነው ደንብ፤ እስከ 50 ሺህ ብር የሚደርስ መቀጮን ጨምሮ በአዲስ አበባ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ተደረገ።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየውጭ ዜጎች በአዲስ አበባ የመኖሪያ ቤት ለመግዛት ከ150 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ያላነሰ ገንዘብ እንደሚያስፈልጋቸው አዲስ መመሪያ ወጣ
አዲስ አበባ የድምፅ ብክለትን በሚፈጥሩ ተቋማት ላይ ከበድ ያለ ቅጣት እጥላለሁ አለች
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"ግሎባላይዜሽን አሉታዊ ጎኑ ከፍ ያለ ነው፤ ብዙ የአፍሪካ ሀገሮች የተማሩ ሰዎቻቸውን በማጣት እየተራቆቱ ነው፤ የሕዝብንም ነፃነት ነጥቋል ማለት ይቻላል" ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ
የምጣኔ ሀብት ተመራማሪ ዶ/ር ፈቃዱ በቀለ፤ የግሎባላይዜሽንን ታራካዊ ዳራ አጣቅሰው፣ በዘርፈ ብዙ ገፅታው እያሳደራቸው ስላሉት ምጣኔ ሀብታዊ፣ የቴክኖሎጂ፣ ሰብዓዊ መብቶች፣ የታዳጊ ሀገራት የአዕምሮ መራቆትና ያደጉ ሀገሮች የአዕምሮ ግኝት፣ የማንነት፣…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየንግድ ማኅበረሰብ አባላት የፌዴራል መንግሥቱ የኢሚግሬሽን ፖሊሲን አስመልክቶ ሁነኛ ለውጦች ከማካሔዱ በፊት በጋራ እንዲመክር ጠየቁ
ፖፕ ሊዮ ሩስያና ዩክሬይን በሚያካሂዱት ጦርነት ሰላማዊ ሰዎችን ዒላማ እንዳያደርጉ አሳሰቡ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየመሬትና ገቢዎች ተቋማትን ጨምሮ በርካታ የመንግሥት ተቋማት ውስጥ ሙስና አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሆነ ማረጋገጡን የፌዴራል ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ
በኢትዮጵያ 79 የሚሆኑ ቋንቋዎች መኖራቸውን በጥናት ማረጋገጡን የባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር ገለጠ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ2026 Census: What you need to know to ensure you’re counted - 2026 የሕዝብ ቆጠራ፤ ስለ መቆጠርዎ እርግጠኛ ለመሆን ማወቅ የሚገባዎ ምንድን ነው?
The 2026 Census is on Tuesday 11 August and every person in Australia on this night must be counted. Census data is used to understand where we live, the…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ#116 Visiting a vet (Med) - #116 Visiting a vet (Med)
Learn English useful for talking about your sick pet. Practise everyday phrases for explaining when an animal is not eating, drinking, or acting normally. -…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛጋዛ ውስጥ በእሥራኤል ጥቃት ለተገደሉ ከመቶ በላይ ፍልስጥኤማውያን የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈፀመ
ጄት ስታር ለሀገር ውስጥና ለዓለም አቀፍ በረራ በእጅ ተያዥ የመንገደኞች ቀላል ሻንጣዎች ላይ የ25 ዶላር ክፍያ ሊጥል ነው
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛከኢትዮጵያ ፈጣን የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ጋር ተመጣጣኝ አዲስ የሥራ ዕድል በበቂ ሁኔታ አለመፈጠሩ ለወጣቶች ከፍተኛ የሥራ አጥነት ጫና እየፈጠረ መሆኑ ተመለከተ
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም "ፋይዳ" ወደ መንግሥት ልማት ድርጅትነት መሸጋገሩን ይፋ አደረገ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየሕዝብ ቆጠራ 2026፤ ዕለተ ቀኑ መቼ ነው? ተቆጣሪዎች እነማን ናቸው? ፋይዳውስ ምንድን ነው?
የአውስትራሊያ ሕዝብ ቆጠራ 2026 ማክሰኞ ኦገስት 11 ምሽት ይካሔዳል። ቆጠራው አውስትራሊያውያንን ብቻ ለይቶ የሚቆጥር ሳይሆን፤ ለጉብኝት አውስትራሊያ ውስጥ የሚገኙትን፣ ዓለም አቀፍ ተማሪዎችንና በጊዜያዊ ቪዛ ያሉትን ሁሉ አካታች ነው።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛድምፃዊና መሰንቆኛ ደርብ ዘነበ ደሳለኝ፤ ከጎንደር እስከ አውስትራሊያ
ድምፃዊና መሰንቆ ተጫዋች ደርብ ዘነበ ደሳለኝ፤ ድምፃዊት እናቱና አኮርዲዮን ተጫዋች አባቱ እንደምን የሙዚቃ ፍቅር አሳድረውበት በአምስት ዓመቱ ማንጎራጎር እንደጀመረ ያወጋል። በሀገረ አውስትራሊያ የሙዚቃ ሕይወቱ ስለ ገጠሙት ተግዳሮቶችና መልካም ዕድሎችም…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛበአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙሉ የራስ ገዝነት መብት የመዋቅር ማስተካከያ ሳቢያ ከ500 በላይ የአስተዳደር ሠራተኞችና 50 መምህራን ያለ ምደባ መቅረታቸው ተመለከተ
ለ21ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የቪዛ መዘግየት በወጣት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ላይ ከፍተኛ ስጋትን መደቀኑ ተነገረ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛHow to answer the 2026 Census English proficiency question | Bonus episode - የ2026 የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ጥያቄን እንደምን መመለስ እንዳለብዎ
How do you choose between "not well", "well" and "very well" when the Census asks about your English? Honorary Professor Lynda Yates explains what these…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ#113 Talking about winter comfort food (Med) - #113 Talking about winter comfort food (Med)
Learn English useful for talking about cosy meals and winter comfort food. Practise everyday phrases for describing cravings, warm meals, and food that makes…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየዋጋ ግሽበት በቁጥጥር ስር አለመዋሉን የፌዴራል መንግሥቱ ገለጠ
ኢራን የሆርሙዝ ሰርጥን ከፈታ አስመልክታ በአዲስ ረቂቅ አጀንዳ ላይ ከኦማን ጋር እየተነጋገረች ነው
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛፕሪሚየር ጃሲንታ አለን ኃላፊነታቸውን ለቀቁ፤ ለምክትል ፕሪሚየር ኃላፊነት ሁለት ዕጩዎች ፉክክር ላይ ናቸው
አውስትራሊያ - ምዕራብ አውስትራሊያ ውስጥ አዲስ ግዙፍ የድፍድፍ ነዳጅ ማጣሪያ ልትገነባ ነው
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ#115 Working on the side (Med) - #115 Working on the side (Med)
Learn English useful for talking about side hustles and earning extra income. Practise everyday phrases for describing additional work, managing…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየቪክቶሪያ ፕሪሚየር ጃሲንታ አላን በፈቃዳቸው ኃላፊነታቸውን እንደማይለቁ አስታወቁ፤ ምክትላቸው በተቀናቃኝነት ቀረቡ
የሊብራል ፓርቲ ምክር ቤት አባል በ2028 ሀገር አቀፍ ምርጫ ወቅት ከዋን ኔሽን ፓርቲ ጋር መቀናጀት ምናልባትም አይቀሬ ሊሆን እንደሚችል ፍንጭ ሰጡ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛበዓለም ባንክ የካርቦን ልቅቀት ቅነሳ ፕሮግራም ከልቅቀት የቀነሰችው ካርቦን ለሽያጭ በማቅረብ ኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሀገር ሆነች
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ በደቡብ ወሎ ሃገረ ስብከት በቦረና ወረዳ፣ በግዮን አባይ ገዳመ አስቄጥስ ቅድስት አርሴማ፣ አቡነ አረጋዊና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶችና የእናቶች አንድነት ገዳም ላይ በደረሰው ጥቃት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ገለጡ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛአውስትራሊያ ቻይና በደቡብ ቻይና ባሕር ላይ የምትከውናቸው እርምጃዎች “ስጋትን ፈጣሪና አደገኛ ድርጊትም ነው” አለች
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በ60 ሀገራት ላይ አዲስ ታሪፍ ሊጥሉ ነው
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛከ100 በላይ የዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት በምክክር ጉባኤው ላይ በመሳተፍ ላይ እንዳሉ ተመለከተ
በኢትዮጵያ የመካንነት ችግር እየጨመረ ነው ተባለ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"ተመራጮች በኢትዮጵያዊነት የሚኮሩ፣ክህሎት ያላቸውና ሁሉንም በሰብዓዊነት የሚመለከቱ ከሆነ ተዓምር ይሠራል፤ ኢትዮጵያዊነታችንን ልንክድ አንችልም" አቶ ንብረት ዓለሙ
አቶ ንብረት ዓለሙ፤ የቪክቶሪያ ኢትዮጵያውያን ማኅበር ዐቃቤ ንዋይ፤ የሥራ ዘመኑ ሊጠናቀቅ የተቃረበውን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ተተኪዎችን ለማስመረጥ ስለ ተመረጠው አስመራጭ ኮሚቴ ተግባራትና ተልዕኮ ያስረዳሉ።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛላ ሮሃ - ስፔይን የፊፋ 2026 የዓለም ዋንጫን አነሳች
ከ104 ፍልሚያዎችና የአንድ ወር አይረሴ የእግር ኳስ ትዝታዎች በኋላ ስፔይን የፊፋ ዓለም ዋንጫ ባለቤት ሆናለች። የ2026 ሻምፒዮናዋ ልብ ሰቃይ ፍልሚያን አካሂዳ የእግር ኳስ ዓለም ድንቅና ብርቁን ዋንጫ ከፍ አድርጋ ለማንሳት የበቃችው አርጀንቲናን 1…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛበኢትዮጵያ የዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንትነት ውድድር ለግል ድርጅቶችና ለኢንዱስትሪ መሪዎች ክፍት ተደረገ
ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (IMF) የኢትዮጵያ የመክፈል አቅም ቢጨምርም፤ አሁንም ከፍተኛ ስጋቶች አሉ አለ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛስፔይን ፈረንሳይን 2 ለ ባዶ ረትታ ለዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ደረሰች
ስፔይን ለፊፋ የዓለም ዋንጫ ውድድር ፍፃሜ ለመድረስ በጨዋታ የበላይነት ጭምር ፈረንሳይን 2 ለ 0 ድል ነስታ የ2026 የዓለም ዋንጫ ባለቤት ለመሆን የአንድ ግጥሚያ ፈሪ ላይ ናት።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2019 የበጀት ዓመት በጀት 502.27 ቢሊዮን ብር ሆኖ ፀደቀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት በኢትዮጵያ ለሚያከናውናቸው ድጋፎች የፖሊሲ ለውጥ ማድረጉ ተገለጠ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ" መጽሐፉ የተለያዩ ቃለምልልሶችንና መጣጥፎችን ቢይዝም፤ የትኛውም የሕብረተሰብ ክፍል በቀላሉ አንብቦ ሊረዳው በሚችል መልክ የተዘጋጀ ነው ። "- ዶ/ር ግርማ አውግቸው ደመቀ
ዶ/ር ግርማ አውግቸው ደመቀ " የኢትዮጵያ ከፑንት እስከ 21ኛው ክፍል ዘመን መጀመሪያ " መጽሐፍ አርታኢ ፤ መጽሐፉ 16 የተለያዩ ቃለ ምልልሶችን እና 10 መጣጥፎችን ያካተተ ነው ብለዋል። ቃለ- ምልልሶቹ በኤስ ቢ ኤስ ራድዮ የአማርኛ ቋንቋ ፕሮግራም…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛHow to get into inclusive football in Australia - “በአውስትራሊያ ሁሉን ሊያስትፍ በሚችለው የእግር ኳስ እንዴት መሳተፍ ይቻላል? ”
It’s no exaggeration when we hear that the FIFA World Cup is bringing the world together. After all, football is known as the world’s most popular sport. But…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛፈረንሳይ፣ ስፔይን፣ አርጀንቲናና እንግሊዝ እንደምን ለዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ተቃረቡ?
ከ48 ሀገራት ብሔራዊ ቡድኖች መካከል አራት ቡድኖች ለዓለም ዋንጫ ፍፃሜ ተቃርበዋል። ፈረንሳይ፣ ስፔይን፣ እንግሊዝና አርጀንቲና ዓይኖቻቸውን ዋንጫይቱ ላይ ጥለዋል።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛዩኒቨርሲቲዎች ዘረኝነትን እንዲፋለሙ ግድ የሚያሰኝ ደንብ ግብር ላይ ዋለ
የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ ዩናይትድ ስቴትስና ኢራን ከግጭት እንዲታቀቡ አሳሰቡ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛThe Torres Strait Islander Flag: Land, Sea and People - “የቶረስ ስትሬት ደሴት ነዋሪዎች ባንዲራ፡ መሬት፣ ባሕር እና ሕዝብ”
In Australia, you might see three flags flying together: the Australian National Flag, the Aboriginal Flag and the Torres Strait Islander Flag. Aboriginal…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛኢሰመኮ፤በቀጣዮቹ ዓመታት ግጭት፣ ሁከት፣ መፈናቀል፣ የሲቪክ ምሕዳርና የሚዲያ ነፃነት ጉዳዮች በሰብዓዊ መብቶች ትግበራ ላይ ዕንቅፋት ሊሆኑበት እንደሚችል ስጋቱን ገለጠ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከሚሰጡት የመኝታ አገልግሎት ላይ አምስት በመቶ የማዘጋጃ ቤት ታክስ እንዲያሰባስቡ ግዴታ የሚጥል ደንብ ተግባራዊ አደረገ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛአርጀንቲና እና ስዊዘርላንድ ለሩብ ፍፃሜ ደረሱ
አርጀንቲና በአስደማሚ ግጥሚያ ከሽንፈት ራሷን ተከላክላ ግብፅን ድል ለመንሳት ስትበቃ፤ ስዊዘርላንድ በአንዲት ግብ ብልጫ ኮሎምቢያን በመለያ ፍፁም ቅጣት ምት ረትታለች።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ" አላማችን በሀዘን ጊዜ መሰባሰብ ብቻ ሳይሆን በደስታውም ጊዜ አብሮ መቆም ነው :: " - ወ/ሮ ቅድስት ሰለሞን
ወ/ሮ ቅድስት ሰለሞን የኢትዮጵያውያን እድር መረዳጃ ማህበር ዋና ጸሀፊ ፤ እድሩ በመጪው ቅዳሜ ከነባር እና አዲስ ከሚገቡት እጩ አባላት ጋር ለመወያየት ጥሪ አድርጓል። እድሩ ላለፉት አስራ ሁለት አመታት ያከናወናቸውን ተግባራት እና የወደፊት እቅዶቹን…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛኖርዊይ ብራዚልን አሰቀቀች፤ ሜክሲኮ ሕልሟ በራሷ ምድር ዕውን ሳይሆን ቀረ
ኖርዌይ ታሪካዊ በሆነ ድሏ የአምስት ጊዘ ሻምፒዮን የሆነችውን ብራዚል ረትታ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሩብ ፍፃሜ አልፋለች። ብራዚልም በፊናዋ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ1990 የዓለም ዋንጫ ወዲህ ለሩብ ፍፃሜ ሳትደርስ ቀርታለች ።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛኢሰመኮ “በትግራይ ክልል ከመንግሥት መዋቅር ውጪ በሚገኝ ታጣቂ ቡድን የሚፈፀም የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ እንደ ጉልበት ብዝበዛና ጦር ወንጀል ሊቆጠር ይችላል” አለ
ኢትዮጵያ የሥጋ ምርቶችን ከዑጋንዳ ማስገባት ጀመረች
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ" ሜክሲኮ በደጋፊዎቿ ፊት ባደርገችው ጨዋታ ድል ቀንቷት ወደ 16ተኛ ዙር አለፈች "
የእግር ኳስ ኮከቦቹ ኤርሊንግ ሃላንድ እና ኪሊያን ምባፔ ፦ እያንዳንዳቸው ሁለት ግቦችን በማስቆጠር ኖርዌይንና፤ ፈረንሳይን ወደ ቀጣዩ ዙር እንዲያልፉ አድርገዋል።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት በዪኔስኮ አምስት ምርጥ የጉዞ መዳረሻዎች ወስጥ ተካተቱ
የትምህርት ሚኒስቴር የክልል ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ራዝ ገዝ እንዲሸጋጋሩ አዲስ ህግ አወጣ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛበኢትዮጵያ መረጃን የከለከለን የመንግስት ሀላፊን እስከ አምስት አመት የሚያስቀጣው አዋጅ በፓርላማ ጸደቀ
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የእናት ጡት ወተት ባንክ በሃዋሳ በይፋ ተከፈተ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛበዮጋንዳ ሁለት የብዙሀን መገናኛዎች በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ትእዛዝ ተዘጉ
አንድ አውስትራሊያዊ በታይላንድ ታዳጊ ወጣት ልጃገረድን ሴት ግድያ ወንጀል ተከሰሰ ፤
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛካናዳ ደቡብ አፍሪካን አሸንፋ ወደ 16 ቡድኖች ዙር የደረሰች የመጀመሪያዋ ቡድን ሆነች
ካናዳ በመጨረሻ ደቂቃ ባስቆጠረችው የድል ጎል የደቡብ አፍሪካን ተስፋ አጨልማ ፤ በዓለም ዋንጫ ታሪኳም የመጀመሪያውን የጥሎ ማለፍ ዙር ድል አስመዝግባለች።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛHow do charities and individual fundraisers work in Australia? - በአውስትራሊያ የእርዳታ እና በግል የሚሰበሰብ ገንዘብ አካሄድ ምን ይመስላል?
What are the rules around raising money and charities? How can you ensure you don't get scammed? Here is what you need to know if you're donating, raising…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ“ የዜማ ደራሲ ብሆንም በግጥሞች ምርጫ ላይ በጣም እጠነቀቃለሁ ። ” - ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ
ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ በዜማ ደራሲንቱ ይበልጥ የሚታወቅ ሲሆን የዜማ ስራውንም አገራዊ ለሆኑ ዘፈኖች በማበርከት ይታወቃል ፤ የሙዚቃ ስራው ቤተሰብ ህይወቱን ከልጆቹ ጋር እንዲጣጥም እንደረዳው ይናገራል ።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ“ ሙዚቃን እንደመዝናኛ ነበር የምጫወተው ፤ ከጀመርኩት ከአስር አመት በኋላ ነው ሙዚቀኛ ነኝ ብዬ የወሰንኩት ። ” - ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ
ድምጻዊ ሚካኤል በላይነህ የዘጠናዎቹዎች ድምውያን ከሚባሉት ተርታ የሚመደብ ሲሆን ለስለስ ባለው የአዘፋፈን ዘይቤው በብዛት ይታወቃል። ሙዚቃን እንደመዝናኛነት ሲጀምር ሙያዬ ይሆናል ብሎ አቅዶ እናደማይውቅ ይናናገራ።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየ2026 ፊፋ የዓለም ዋንጫ ግጥሚያዎች ትንታኔ በቀድሞዎቹ የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን ተጫዋቾች ኤርሚያስ ወንድሙ እና ኤልያስ ጃዋር አንደበት
የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ እግር ኳስ ቡድን አጥቂ፣ የጥቁር አንበሳ፣ የመድንና መብራት ኃይል ተጫዋች ኤርሚያስ ውንድሙ እና ኤልያስ ጃዋር፤ የቀድሞው መብራት ኃይል፣ የኢትዮጵያ ወጣትና ብሔራዊ ቡድን አጥቂ፤ የዘንድሮውን 2026 የዓለም ዋንጫ ግጥሚያዎች…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛሮናልዶ በስድስት የዓለም ዋንጫዎች ግቦችን በማስቆጠር የመጀመሪያው ተጫዋች ሆነ
ለክሪስቲያኖ ሮናልዶ ሬኮርድን ያስመዘገበው፣ ለሉካ ክብረ ወሰንን ያስጨበጠውና እንግሊዝን ለብስጭት የዳረገው የ2026 የፊፋ ዓለም ዋንጫ 13ኛ ቀን የፍልሚያ ውሎ ጥንቅር።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛበኢትዮጵያ ከ5,000 በላይ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ቢኖሩም የንብረት ምዝገባ ያደረጉት 12 በመቶ ብቻ መሆናቸውን የፌዴራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት አስታወቀ
ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 13 መቀመጫዎችን ያገኘው ኢዜማ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች አብዛኛውን ድምፅ ያገኘ ሆነ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"በየትኛውም የኢትዮጵያ ግዛት እንደ ሐረር የታላላቅ ሰዎች አፅም ያረፈበትና የሚታወስ ቦታ የለም" አቶ ተሾመ ብርሃኑ ከማል
አንጋፋ ጋዜጠኛ፣ ደራሲ፣ የእስልምና ጉዳዮች ተመራማሪና የታሪክ አጥኚ አቶ ተሾመ ከማል ብርሃኑ፤ በቅርቡ "Keepers of a Sacred Civilisation" በሚል ርዕስ ስለ ሙስሊም የሐረር ሴት ቅድስቶች ታሪክ አጣቅሰው የፃፉትን መጣጥፍ አስመልክተው…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"ሙስሊም ቅዱሳን የቅድስና ማዕረግ የሚያገኙት ከማኅበረሰቡ ነው፤ ከክርስትናው ይለያል።" አቶ ተሾመ ብርሃኑ ከማል
አንጋፋ ጋዜጠኛ፣ ደራሲ፣ የእስልምና ጉዳዮች ተመራማሪና የታሪክ አጥኚ አቶ ተሾመ ከማል ብርሃኑ፤ በቅርቡ "Keepers of a Sacred Civilisation" በሚል ርዕስ ስለ ሙስሊም የሐረር ሴት ቅድስቶች ታሪክ አጣቅሰው የፃፉትን መጣጥፍ አስመልክተው…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ውጤት ይፋ አደረገ
ኢትዮጵያ በቅርብ ዓመታት ውስጥ Laptop እና iPad ማምረት እንደምትጀምር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛስፔይን አንሰራራች፤ ካቦ ቬርዴ በዓለም ዋንጫ ታሪክ አስመዘገበች
ስፔይን ወደ ቡድን H የመጀመሪያ መሰላል ላይ ስትወጣ፤ ካቦ ቬርዴ በፊናዋ በዓለም ዋንጫ ተሳትፎ ታሪኳ ከዩራጓይ ጋር አቻ ያስወጣትን ግቦች በማስቆጠር የራሷን ታሪክ ፃፈች።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛበሜልበርን አራት አድባራት የ'ፍትሕ ለአርሲ' ጥያቄ አቀረቡ፤ የአቋም መግለጫም አወጡ
በሜልበርን አራት አድባራትን ያቀፈ የሀገረ ስብከት ፅሕፈት ቤትና የካሕናት ኅብረት "ታላቅ የሐዘንና የምክክር ቀን" ሲል ቅዳሜ ሰኔ 13 / ጁን 20 በሜልበርንና አካባቢዋ ለሚገኙ ምዕመናንና ምዕመናት ባዘጋጀው የውይይት መድረክ በመቶዎች የሚቆጠሩ…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየዓለም ዋንጫ 6ኛ ቀን ውሎ፤ ሜሲና የዓለም ምርጥ እግር ኳስ ተጫዋቾች አስደናቂ ሪኮርዶችን አስመዝግበዋል
በ2026 የፊፋ ዓለም ዋንጫ ውድድሮች 6ኛ ቀን ሬኮርዶች ተሰብረዋል፤ ልዕለ ኮከብ ተጫዋቾች ድንቅ ወሳኝ ግቦችን አስቆጥረዋል።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየዜጎች የግል መረጃ ለምርመራና ለደህንነት ተግባራት እንዳይውል የሚከለክል አዲስ የስታቲስቲክስ ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን 'በመጨረሻ የምክክር ምዕራፍ ላይ ብንሆንም ፤ አካታች የምክክር ጉባኤ ለማካሔድ በማንኛውም ጊዜ ወደ ምክክሩ ለሚመጡ አካላት በሬ ክፍት ነው' አለ።