Shows / SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Episodes
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ#96 At a swimming lesson (Med) - #96 At a swimming lesson (Med)
Learn how to talk about swimming in English. - Learn how to talk about swimming in English.
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ በሱዳን ጎርፍ አስከትሏል በሚል በግብፅ የቀረበባትን ክስ ውድቅ አደረገች
በአማራ ክልል በባሕላዊ መንገድ ግጭቶች የሚፈቱባቸው የባሕል ፍርድ ቤቶች ሥራ ጀመሩ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ#95 Under the stars (Med) - #95 Under the stars (Med)
Learn how to talk about the night sky and stargazing. - Learn how to talk about the night sky and stargazing.
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"ኢትዮጵያ ለእኔ ቤቴ ናት፤ ሀገሬ ናት። የትም ልሂድ የት፤ ወደ ቤቴ፣ ወደ ሀገሬ ልመለስ የምለው እናት ኢትዮጵያን ነው" ድምፃዊ ቫሔ ታልቢያን
ድምፃዊ፣ ሙዚቃ ቀማሪና የዳንስ መምህር ቫሔ ታልቢያ፤ ስለማንነት ጥያቄና ስለ ወደፊት የሙዚቃ ሕይወት ትልሞቹ ይናገራል። "በኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ወደ አውስትራሊያ ተጋብዞ የመምጣት ዕድል ካለ ለእኔ በጣም ትልቅ ክብር ነው' ይላል።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"ኢሬቻን ወደፊት ለሚያከብሩት እግዚአብሔር ያድርሳችሁ! ላከበሩትም እንኳን አደረሳችሁ!" ኦቦ ዓለማየሁ ቁቤ
የኢሬቻ መልካ 2018 / 2025 ክብረ በዓል እሑድ መስከረም 18 / ሴፕቴምበር 28 በ Wilson Botanic Park Berwick ሜልበርን ተከብሮ ውሏል። ታዳሚዎች የበዓሉን አከባበር አስመልክተው አተያዮቻቸውን ያጋራሉ። መልካም ምኞቶቻቸውንም…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛድምፃዊ ቫሔ ቲልቢያን፤ ከምዕራብ አርመንያ እስከ ኢትዮጵያ
ቫሔ ቲልቢያን፤ ኢትዮጵያዊ - አርመንያዊ ድምፃዊ፣ ሙዚቃ ቀማሪና ለዓለም አቀፍ የዳንስ መድረክ የበቃ ነው። አርመንያን፣ ኢትዮጵያንና ድፍን አኅጉሪቱን አፍሪካን ወክሎ በ2015 ዩሮ-ቪዢን የሙዚቃ ውድድር ላይ ተሳትፏል። ኢትዮጵያ እንደምን ከጥንታዊቷ…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየመጀመሪያ ጊዜ ቤት ገዢዎች የአምስት ፐርሰንት ተቀማጭ ፖሊሲና የአረጋውያን ክብካቤ ሠራተኞች ደመወዝ ጭማሪ ከዛሬ ኦክቶበር 1 ጀምሮ ግብር ላይ ውለዋል
አውስትራሊያ ከእሥራኤል ጋር ያላት የመከላከያ ውሎች እንድታቋርጥ ዳግም ጥሪ ቀረበ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛበትግራይ ክልል የወባ በሽታ በወረርሽኝ መልክ መከሰቱ ተነገረ
ኢትዮጵያ የአንድ ቢሊዮን ዶላር የዩሮ ቦንድ አበዳሪዎች ዕዳዋን በአዲስ መልክ እንዲያዋቅሩላት ፓሪስ ላይ እየተነጋገረች ነው
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ“ በአውስትራሊያ ያሉት የበጎ ፈቃድ አገልጋዮች ያደረጉት አስተዋፅዖ ታላቅ ነው፤ የበርካታ ታዳጊዎችን ሕይወት ለውጠዋል” የብሬቭኸርትስ ኢትዮጵያ አባላት
ወ/ሮ ቆንጂት ጥላሁን የብሬቭኸርትስ ኢትዮጵያ መሥራች እና ዳይሬክተር ፤ የብሬቭኸርትስ የቦርድ አባላት እና የበጎ ፈቃድ አገልጋዮች ማርታ ቦረና ፤ ወ/ሮ ብርቱካን ቢያድግልኝ እና ወጣት ጊፍቲ በቀለ 'ብሬቭኸርትስ ኢትዮጵያውያንን ለመርዳት በኢትዮጵያውያን…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ“ ኑ እና አብረን እራት እንብላ ፤ ወገኖቻችንንም እንርዳ "- የብሬቭኸርትስ ኢትዮጵያ አባላት
ወ/ሮ ቆንጂት ጥላሁን የብሬቭኸርትስ ኢትዮጵያ መሥራች እና ዳይሬክተር ፤ የብሬቭኸርትስ የቦርድ አባላት እና የበጎ ፈቃድ አገልጋዮች ማርታ ቦረና ፤ ወ/ሮ ብርቱካን ቢያድግልኝ እና ወጣት ጊፍቲ በቀለ ፤ ብሬቭኸርትስ ላለፉት አሥራ አንድ ዓመታት በኢትዮጵያ…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛአውስትራሊያ የዶናልድ ትራምፕን ባለ 20 ነጥብ የጋዛ የሰላም ዕቅድ እንደምትደግፍ አስታወቀች
የአውስትራሊያ ብሔራዊ ባንክ የወለድ መጠን ባለበት ረግቶ እንዲቆይ ወሰነ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"የስኳር በሽታ ሕመምተኞች ከሌሎች ሰዎች በበለጠ ከ2 እስከ 5 እጥፍ በላይ ለልብ ድካም ተጋላጭነታቸው ከፍተኛ ነው" ጌታእንዳለ ዘለቀ
ጌታእንዳለ ዘለቀ ነገራ፤ የልብ ሕመም ምርምር ሳይንቲስት ናቸው። በስኳር ሕመም አስባብ የሚከሰትን የልብ ድካም አስመልክተው ያቀረቡት የጥናታዊ ምርምር ግኝታቸው ከአሜሪካ የልብ ማኅበር የ Paul Dudley White International Scholar…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኑክሊየር ምሕንድስና ትምህርት በዘንድሮ የትምህርት ዘመን ሊጀመር ነው
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአዕምሯዊ ንብረት ወጣቶች ድርጅት ዓመታዊ የፈጠራ ሪፖርት ኢትዮጵያ ከ139 ሀገሮች 134ኛ ደረጃ ላይ ተመደበች
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ" እንኳን ለደመራ እና መስቀል በአል በሰላም አደረሳችሁ ። " - መጋቢ አእላፍ ቀሲስ በቃሉ ዳዊት
መጋቢ አእላፍ ቀሲስ በቃሉ ዳዊት በሜልበርን ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ የደመራ እና የመስቀል በአል ሀይማኖታዊ እና ባህላዊ አንድምታ አስረድተዋል ።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"የኤሌክትሪክ መኪናዎች ወደ ኢትዮጵያ መግባት መሠረተ ልማትን ለመሥራት ያስገድዳል፤ ወደ ፈጠራ ይመራል። የኤሌክትሪክ ስኩተርና ብስክሌትም አሥፈላጊ ናቸው"ዶ/ር ፀጋዬ ደግነህ
ዶ/ር ፀጋዬ ደግነህ፤ የምጣኔ ሃብትና አስተዳደር ባለሙያ፣ በጀርመን የመኪና ኩባንያ የዘላቂ ልማትና ብዝኅነት ሥራ አስኪያጅ፤ የኤሌክትሪክ መኪና፣ ስኩተርና ብስክሌት ለኢትዮጵያ ያለውን ጠቀሜታ ከጀርመንና ቻይና ተሞክሮ ጋር አያይዘው ያስረዳሉ።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"የኤሌክትሪክ መኪናዎች ለመንዳት ምቹና ለአካባቢያዊ አየር ብክለት ቅነሳ ጠቀሜታ ቢኖራቸውም፤ ጉዳትም አላቸው" ዶ/ር ፀጋዬ ደግነህ
ዶ/ር ፀጋዬ ደግነህ፤ የምጣኔ ሃብትና አስተዳደር ባለሙያ፣ በጀርመን የመኪና ኩባንያ የዘላቂ ልማትና ብዝኅነት ሥራ አስኪያጅ፤ ከነዳጅና ናፍጣ ወደ ኤሌክትሪክ ኃይል መኪና ሽግግርን ፋይዳዎች በንፅፅሮሽ አንስተው ያስረዳሉ።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛኢሬቻ መልካ በሜልበርን - አውስትራሊያ እሑድ ዕለት ሊከበር ነው
የኢሬቻ ክብረ በዓል አዘጋጅ ኮሚቴ አባላት ኦቦ አብደታ ሆማ እና ኦቦ በንቲ ኦሊቃ፤ እሑድ መስከረም 18 / ሴፕቴምበር 28 በ Wilson Botanic Park Berwick ተከብሮ ስለሚውለው የኢሬቻ ክብረ በዓል ሥነ ሥርዓትና ሂደት ይናገራሉ። የአብረን…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ“ የተቀበልኳቸው ታላላቅ ሽልማቶች እና እውቅናዎች ተጨማሪ ሀላፊነትን መሸከም እና ጠንክሬ መስራት እንዳለብኝ የሚያስታውሱ ናቸው። ” - አርቲስት ሮፍናን
አባቴ በእኔ ስኬት ውስጥ ታላቅ ስፍራ አለው ፤ ዩኒቨርሳል ሙዚቃ ያቀረበልኝን ውል ስፈርም በእነሱ ቅድመ ሁኔታ ስይሆን በእኔ ምርጫ የተሻለ ውል እንድፈርም የረዳኝ የአባቴን ምክር እና የሕይወት ፍልስፍና መስማቴም መከተሌም ነው ፤ ይለናል ሁለገቡ…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"ደሲ ለእግዚአብሔር ቃልና ለፍቅር የተረታች ናት፤ በሕልፈቷ ድንጋጤ ውስጥ ነው ያለሁት፤ ያለ እሷ እንዴት እንደምኖር አላውቅም" የፓስተር ደሲ ባለቤት አቶ ዓይናለም ካሱ
የመንፈሳዊ ሕይወትና የበጎ አድራጎት አገልጋይዋ ፓስተር ደሲ ባይሳ ከእዚህ ዓለም በሕልፈት ተሰናብተዋል። "አታልቅስ፤ ነገ ይነጋል" ነበር የመጨረሻ ቃሏ ያሉትን ታላቅ ወንድማቸውን ተክሉ ባይሳ አክሎ፤ ቤተስብና ወዳጆች ጥልቅ ሐዘናቸውን ይገልጣሉ።…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ“ራሴን ማድመጤ የተሻለ ሙዚቃን ይዤ እንድመጣ ረድቶኛል ፤ በራሴ መንገድ የመጣሁበት ሙዚቃ ፍሬውን ሳይ እድለኛ ነኝ እንድል ያደርገኛል -አርቲስት ሮፍናን
የሙዚቀኛ ውጤት የሚታየው በሙዚቀኛው ጥረት ብቻ ሳይሆን በማህበረሰቡ የአስተሳሰብ አቅጣጫ ነው ። አገር ሰላም ሲሆን ማህበረሰብ ሲራጋጋ የኪነ- ጥበብ ባለሙያዎችም ጥሩ ስራን ይዘን መቅረብ እንችላላን፤ የሚለን የሙዚቃ ስራውን በአውስትራሊያ እያሳየ ያለው…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ- አንቶኒ አልበኒዚ ከአሜሪካው ፕሬዝደንት ጋር በጥቅምት ወር ሊገናኙ ቀጥሮ ተቆረጠ
አንቶኒዮ ጉተሬዝ በጋዛ የእስራኤልን ወረራን ተቃወሙ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"የአዲስ ዓመት ዝግጅቱ ሀገር ቤት ያሳለፍናቸውን ጥሩ ጊዜዎች እንድናስታውስ አድርጎናል፤ መበረታትና መጠናከር ያለበት ነው፤ መልካም አዲስ ዓመት!" ዶ/ር አደራጀው ተሾመ
የኢትዮጵያውያን 2018 አዲስ ዓመት አከባበር በኬንሲንግተን ማዘጋጃ ቤት አዳራሽ ሜልበርን አውስትራሊያ።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛዜና -አውስትራሊያዊቷ የከፍታ ዘላይ ኒኮላ ኦላሳርገን የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆነች
እስራኤል የፍርስጤማውያንን ነጻ አገር የመሆን ጥያቄ መቼውንም ቢሆን እውቅናን አልሰጥም አለች፤
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛአገርኛ ሪፖርት - " ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የባህር በር የመፈለግ መብቷን እንደግፋለን" - የሶማሌው ፕሬዝደንት ሀሰን ሼክ መሀመድ
" ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የባህር በር የመፈለግ መብቷን እንደግፋለን" - የሶማሌው ፕሬዝደንት ሀሰን ሼክ መሀመድ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"ነቢይ አይደለሁም፤ ነቢይ እንዳልባል እንጂ ሁለቱም [ኢትዮጵያና ኤርትራ] ተለያይተው የሚኖሩ አይመስልም" ብርጋዲየር ጄኔራል ውበቱ ፀጋዬ
በሕይወት ዘመናቸው "ኤርትራውያን ጀግናዎች ናቸው፤ ጥሩ ተዋጊዎች ናቸው። ለኢትዮጵያ ደማቸውን አፍስሰዋል፤ በኢትዮጵያ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ ስር ወድቀዋል። "አንድነት ኢትዮጵያ" ብለው የሔዱ ናቸው" ያሉን የቀድሞው የሁለተኛው አብዮታዊ…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"ባሕላችን ለትውልድ እንዲቀጥል ወላጆች ልጆቻቸውን ይዘው መጥተው ስለ ኢትዮጵያ አዲስ ዓመት እንዲያስረዱ ጥሪያችንን እናቀርባለን" ወ/ት ገነት ማስረሻ
ወ/ት ገነት ማስረሻ፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ምክትል ፕሬዚደንት፤ ቅዳሜ መስከረም 10 / ሴፕቴምበር 20 በ Kensington Town Hall በማኅበሩ አስተባባሪነት ስለሚከበረው የ2018 አዲስ ዓመት ልዩ ዝግጅት ይገልጣሉ።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛአውስትራሊያን አክሎ 42 ሀገራት በኢትዮጵያ የተጀመረው የሽግግር ፍትሕ ሂደት ባለበት መቆሙና የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ እንዳሳሰባቸው ለተመድ አስታወቁ
እስከ አንድ ወር ጊዜ ይወስድ የነበረውን አዲስ የንግድ ምዝገባና ዕድሳት አሠራርን ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል በመቀየር በሁለት ቀናት መጨረስ የሚያስችል ሥርዓት ይፋ ተደረገ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"የእኛ ዕድር ከዘርና ሃይማኖት ነፃ የሆነ ነው፤ ኑ ተደጋግፈን ማኅበራዊ ሕይወታችንን እናጎልበት፤ መልካም አዲስ ዓመት" የኢትዮ-አውስትራሊያ አንድነት መረዳጃ ዕድር
የኢትዮ - አውስትራሊያ አንድነት ዕድር ሰብሳቢ አቶ መስቀሉ ደሴ፣ ፀሐፊ ብሩክ ይማ እና የበዓል አስተባባሪ ወ/ሮ ጥሩወርቅ ይልማ፤ ቅዳሜ መስከረም 10 / ሴፕቴምበር 20 የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት 2018 እና የመስቀል በዓል በጣምራ ከኢትዮጵያውያንና…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየጥምር ዜግነት ጉዳይ በአጀንዳነት ለኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ቀረበ
የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሔደው ጦርነት ሳቢያ በኢትዮጵያ ላይ ጥለውት የነበረውን የተለያዩ ዕቀባዎችን የያዘው ፕሬዚደንታዊ ትዕዛዝ፤ በፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ለተጨማሪ አንድ ዓመት ፀንቶ እንዲቆይ ተወሰነ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"ኢትዮጵያ ውስጥ የሁሉንም ክልልሎች ይሁንታ ለማግኘትና ዲሞክራሲም ሥር እንዲሰድ ለማድረግ ፕሬዚደንታዊ ሥርዓት ያስፈልጋል" ዶ/ር ሰለሞን ኃይለማርያም
ዶ/ር ሰለሞን ኃይለማርያም፤ ስለምን የሶስተኛ ዲግሪ የመመረቂያ የምርምር ፅሁፋቸውን ከዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ አውጥተው "Ethiopian Elites' Political Cultures: a critical juncture: The cases of Amhara…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"የዳያስፖራ ማኅበረሰብ ውስጥ የሚታየው የሀገር ቤት ነፀብራቅ ነው፤ ሀገር ቤት ያለው ሁኔታ እየሰከነ ሲሄድ የዳያስፖራውም እንደዚያ ይሆናል" ዶ/ር ሰለሞን ኃይለማርያም
የ "Ethiopian Elites' Political Cultures: a critical juncture: The cases of Amhara, Oromo and Tigray" መፅሐፍ ደራሲ ዶ/ር ሰለሞን ኃይለማርያም፤ መፅሐፋቸው ውስጥ ያሠፈሯቸውን አንኳር ምክረ…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"የኢኮኖሚ ዕድገት ኢትዮጵያዊነት እንዲለመልም ያደርጋል፤ ሕዝብ ኢትዮጵያዊነት የሚያስገኘውን ጥቅም እንዲያውቅ ማድረግ ያስፈልጋል" ዶ/ር ሰለሞን ኃይለማርያም
ዶ/ር ሰለሞን ኃይለማርያም፤ "Ethiopian Elites' Political Cultures: a critical juncture: The cases of Amhara, Oromo and Tigray" በሚል ርዕሰ ለሕትመት ስላበቁት መፅሐፋቸው ዋነኛ ይዘቶች ይናገራሉ።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ2018 - አዲስ ዓመት፣ አውደ ዓመት፣ ዕንቁጣጣሽ
የ"ክብረ በዓላት፤ ሃይማኖትና ባሕል" መፅሐፍ ደራሲ መላኩ ጌታቸው፤ ስለ ኢትዮጵያ ታሪካዊ የዘመን ቅመራና ባሕላዊ አከባበር ያስረዳል።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"አዲሱ አመት የአንድነት ፤ የመተባበር ፤ የሰላም እና ፍቅር እንዲሆንልን እንጸልያለን " - ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ
ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አባልና በኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብክት ሊቀ ጳጳስ አዲሱ አመት የአንድነት ፤ የመተባበር ፤ የሰላም እና ፍቅር እንዲሆንልን እንጸልያለን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ" አዲሱ ዓመት ወደ እግዚአብሔር የምንጠጋበት እና የምንታደስበት እንዲሆን እፀልያለሁ" - ዶ/ር ናትናኤል ገመዳ
ዶ/ር ናትናኤል ገመዳ - በዘፀአት የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ፓስተር፤ አዲሱ ዓመት ወደ እግዚአብሔር የምንጠጋብት እና የምንታደስበት እንዲሆን እፀልያለሁ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ" አዲሱ አመት የፍቅር ፤ የመቻቻል ፤ የሰላም እና ከድህነት የምንወጣበት ይሁንልን "- ሼህ አብዱራህማን
ሼህ አብዱራህማን ሀጂ ከቢር በአውስትራሊይ የእስልምና እምነት ተከታዮች መሪ አዲሱ የ2018 አመተ ምህረት የፍቅር ፤ የመቻቻል ፤ የሰላም እና ከድህነት የምንወጣበት ይሁንልን ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል ።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"ዕንቁጣጣሽ ወዳጅነትና ክብር በተመላበት መልኩ ሁሉንም የማሰባሰቢያ ጊዜ ነው፤የእናንተ ስኬት የአውስትራሊያ ስኬት ነው፤መልካም አዲስ ዓመት!" የተቃዋሚ ቡድን መሪ ሱዛን ሊይ
የአውስትራሊያ ፌዴራል ተቃዋሚ ቡድን መሪ ሱዛን ሊይ፤ ለኢትዮጵያውያን - አውስትራሊያውያን እንኳን ለ2018 አዲስ ዓመት አደረሳችሁ ሙሉ መልዕክት።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"ኢትዮጵያዊነት ልዩ ኩራታችን ነው፤ ይህን አዲስ ዓመት ለሀገራችን ኢትዮጵያና ለልጆቿ የሰላም፣ የጤናና የሕዳሴ ያድርግልን" ልዑል ኤርሚያስ ሳህለ ሥላሴ
"አንድ ስንሆን፤ ሳንለያይ ብዙ መስራት እንደምንችል ይህ [ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ] ትልቅ ምሳሌ ነው። እግዚአብሔርም የግርማዊ ጃንሆይን ሕልም ተሠርቶ ስላሳየን ስሙ ምስጉን ይሁን" ልዑል ኤርሚያስ ሳህለ ሥላሴ ኃይለ ሥላሴ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየአባቶች ቀን አከባበር በሀገረ አውስትራሊያ
አቶ ጉግሳ አሊጋዝ "ለኢትዮጵያውያን ሁሌም የአባቶች ቀን ነው። እኛ ጥሩ አባቶች ነን። ልጆቼን እጅግ በጣም ነው የምወዳቸው፤ በእዚህ ምድር ላይ በጣም ያስደሰተኝ ነገር ቢኖር ከልጆቼ ጋር ያሳለፍኩት ጊዜ ነው " ሲሉ፤ አቶ ኃይለማርያም ኃይለየሱስ…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"አዲሱን ዓመት ስናከብር በአንድነቷ የጠነከረች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስተላለፍ ጠንክራችሁ የምትቀጥሉበት ዓመት እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ" አምባሳደር አንዋር ሙክታር
አኑዋር ሙክታር፤ በአውስትራሊያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተጠባባቂ አምባሳደር፤ የ2018 የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ 233 ቢሊየን ብር ወጪ መደረጉን የኢትዮጵያ መብራት ኃይል አስታወቀ
በሰሜን ጎንደር ዞን ድርቅ ስጋት ማስከተሉ ተመለከተ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየቀን መቁጠሪያችን የማንነታችንን መገለጫ እሴቶቻችን አንዱ ነው ፤ ይህንንም ቤ/ክ ብቻ ሳትሆን መላው ኢትዮጵያውያን የማስጠብቅ ሀላፊነት አለብን
ከኢትዮጵያውያን ማንንት መገለጫ አንዱ ልዩ የሆነ የቀን መቁጠሪያችን ነው ። ምንጩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ ቢሆንም አገልግሎቱ ግን ለመላው ኢትዮጵያውያን ነው በዚህም ልንኮራ ይገባናል፤ የሚሉን መጋቢ ምስጢር ቀሲስ ስንታየሁ በምስራቅ…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየጳጉሚት ወር በአትዮጵያውያን የቀን መቁጠሪያ የአመቱን ትርፍ ቀናት ሸክፋ የያዘች ልዩ ወር ናት ።
መጋቢ ምስጢር ቀሲስ ስንታየሁ በምስራቅ አውስትራሊያ ሀገረ ስብከት የሜልበርን ምእራፈ ቅዱሳን ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያ አስተዳዳሪ ፤ እንዲሁም መጋቢ ጥበብ ቀሲስ ቴዎድሮስ በሜልበርን ደብረገነት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አገልጋይ የጳጉሜ ወር…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ#94 Talking about autism (Med) - #94 Talking about autism (Med)
Learn how to talk about Autism Spectrum Disorder respectfully. Understand common autism symptoms and use simple language to describe autism in everyday…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"ለኢትዮጵያውያን ሁሉ መጪው ዘመን ከትናንት የተሻለ፣ ሀገራችን ገናናነቷ ጎልቶ የሚወጣበትና አብረን የምንቆምበት እንዲሆን እመኛለሁ" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ፕሬዚደንት፤ የ2018 የኢትዮጵያ አዲስ ዓመትን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"ለመላ ኢትዮጵያውያን መልካም አዲስ ዓመት! አብረን እናሳልፍ፤ አንድ ጎረቤት አንድ ጓደኛ ይዛችሁ ኑ፤ በባሕላችሁ ተደሰቱ!" የአዲስ ዓመት ቅበላ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት
አቶ ካሪም ደጋል፣ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ክብረ በዓል አስተባባሪ ኮሚቴ ዳይሬክተር፤ አቶ ኃይለሰማዕት መርሃጥበብ፣ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ዋና ፀሐፊና የአዲስ ዓመት አስተባባሪ ኮሚቴ አባል፤ ወ/ሮ ማርታ ከበደ፤ የአዲስ ዓመት አስተባባሪ…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት ልዩ ዝግጅት ፉትስክሬይ ላይ ማድረጋችን፤ የሕዝባችን ሱቆችና ንግዶች ብዛቱና የመገናኛ ቦታው ፉትስክሬይ ስለሆነ ነው" ዳይሬክተር ካሪም ደጋል
አቶ ካሪም ደጋል፣ የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ክብረ በዓል አስተባባሪ ኮሚቴ ዳይሬክተር፤ አቶ ኃይለሰማዕት መርሃጥበብ፣ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበር ዋና ፀሐፊና የአዲስ ዓመት አስተባባሪ ኮሚቴ አባል፤ ወ/ሮ ማርታ ከበደ፤ የአዲስ ዓመት አስተባባሪ…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየታላቁ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ 46 በመቶ የሚሆነውንና የኤሌክትሪክ ኃይል የማያገኘውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ገለጠ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለዳያስፖራ ማኅበረሰብ 50 ቢሊዮን ብር የብድር አገልግሎት አዘጋጅቻለሁ አለ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየፀረ ፍልስተኞች የተቃውሞ ሰልፍ ውግዘት ደረሰበት
የትራምፕ አስተዳደር ፍልስጥኤማውያንን የቤት ኪራይ ገንዘብ ሰጥቶ ከጋዛ ለማስወጣት መወጠኑ ተጠቆመ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛታላቁ የሕዳሴ ግድብ ጳጉሜን 4 ቀን ይመረቃል ተባለ
የቦይንግ ኩባንያ አዲሱ የአውሮፕላኑ ሞዴል በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የበረራ ፍተሻ ይደረግለታል አለ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛሀገራዊ ቃል ኪዳን "ባለቤቴን ለትዳር ስጠይቃት 'እኔ ሀገሬ ላይ ነው መኖር የምፈልገው፤የአንቺ ሃሳብ ምንድነው? ይህን ማወቅ አለብኝ አልኳት' ዳንኤል አለማር
ዳንኤል አለማር፤ በቀዳሚው ክፍለ ዝግጅታችን የግለ ታሪክ ወጉ እንደምን በለጋ የወጣትነት ዘመኑ ከእነ ቤተሰቡ ለሀገረ ኬንያ የስደት ሕይወት እንደበቃና እንደተወጣው አውግቷል። በመቋጫው፤ የአውስትራሊ አዲስ የሕይወት ምዕራፍ ጅማሮውን፣ ተግዳሮቶችና መልካም…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"ለዛሬ መድረሻዬ ሆነኝ የምለው፤ በስደት ካምፕ የነበረኝና የሰንቅኩት ሕይወት ነው" ዳንኤል አለማር
"የኃይለ ሥላሴ ቤተሰብ ነው እንዳትነኩት" - ዳንኤል አለማር፤ በግለ ታሪክ ወጉ ገና ለአካለ መጠን ሳይደርስ በለጋ ዕድሜው ከእናትና ወንድሞቹ ጋር እንደምን የትውልድ ሀገሩን ኢትዮጵያን ለቅቆ ለኬንያ የስደት ካምፕ እንደተዳረገና የኢትዮጵያ ስም እንደምን…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛዓለም አቀፍ በረራዎች ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በመቀሌ፣ ባሕርዳርና ድሬዳዋ አውሮፕላን ማረፊያዎች ሊጀመር ነው
የግዕዝ ቋንቋ ከመጪው የትምህርት ዘመን ጀምሮ በአማራ ክልል ከሶስተኛ ክፍል በመጀመር እንደሚሰጥ ተገለጠ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"የአሸንዳ በዓል ሃይማኖታዊም ባሕላዊም ነው፤ ክብርና ልጅነታችንን ያስታውሳል፤ የሴቶች በዓል በመሆኑ የነፃነታችን በዓል ነው" ነርስ ሰላማዊት ደሞዝ
በተለይ የሴቶች ልዩ በዓል የሆነው ሀገር በቀሉ የአሸንዳ ክብረ በዓል በሜልበርን አውስትራሊያ ቅዳሜ ነሐሴ 17 / ኦገስት 23 በትግራይ ማኅበረሰብ አባላት ዘንድ በሐሴት ተመልቶ፤ በድምቀት ተከብሮ ውሏል። በቪክቶሪያ የትግራይ ሴቶች ማኅበር አመራር…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛኢትዮጵያ ውስጥ ኢ-ሲጋራ የሚያጤሱ ሴቶች ቁጥር እየጨመረ ነው፤ 32 በመቶ የሚሆነው የማኅበረሰብ ክፍልም ሱስ ውስጥ ይገኛል
የውጭ ዜጎች በመንግሥት የሕክምና ተቋማት ለሚያገኙት የሕክምና አገልግሎት በእጥፍ እንዲከፍሉ የሚያስገድድ መመሪያ ተዘጋጀ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"ትዝታ ትናንትን በምልስት በማውሳት ዛሬ ላይ ሕይወት ዘርተን የምናቆየው ነው፤ ለፊልሜ መጠሪያ ያደረግኩትም ቃለ መልዕክቱ ለልብና ለነፍስ ስለሆነ ነው"አራማዝት ካላይጂያን
የ"ትዝታ" ዘጋቢ ፊልም ዳይሬክተር አራማዝት ካላይጂያን፤ አርመንያውያን በኢትዮጵያ ሙዚቃ ዓለም ውስጥ ከሠልፈኛ ባንድ ምሥረታ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር ቀማሪነትና የዘመናዊ ሙዚቃ ጉልህ የጥበብ አሻራዎቻቸውን ስለሚዘክረው ፊልማቸው ጭብጦች ያወጋሉ።…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ#93 Bragging about your car (Med) - #93 Bragging about your car (Med)
Learn how to talk about cars and understand common Aussie car slang. - Learn how to talk about cars and understand common Aussie car slang.
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምጣኔ 15 በመቶ ሆኖ እንደሚቀጥል የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር የመግቢያ ቲኬት ዋጋ ጭማሪ አደረገ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ1934 - 2017፤ የተዋናይ ደበበ እሸቱ ዕረፍት
ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ ሰው ሠራሽ አስተውሎት በነገው ዕለት ለሚጀመረው የምርታማነት ጉባኤ ዋነኛ ትኩረት መሆኑን አመላከቱ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ 49 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች ብቻ የባንክ ሂሳብ እንዳላቸው ተገለጠ
በአፋር ክልል 2.6 ሚሊዮን ዓመት ያስቆጠረ የሰው ቅሪተ አካል ተገኘ