Shows / SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ
Independent news and stories from SBS Audio, connecting you to life in Australia and Amharic-speaking Australians. - ያልወገኑ ዜናዎችን ያቀርብልዎታል። ከአውስትራሊያ የሕይወት ታሪኮችና አማርኛ ተናጋሪ አውስትራሊያውያን ጋር ያገናኝዎታል።
Episodes
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ የሌበር ፓርቲ ለዳግም ምርጫ ድል የበቃው የ 'ተራማጅ አርበኛነት' አቋምን በማራመድ እንደሁ አመላከቱ
ፕሪሚየር ጀርሚ ሮክሊፍ ክፍለ ሀገራዊ ምርጫ እንዲካሔድ የታዝማኒያን እንደራሴ ጠየቁ

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"አውስትራሊያ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ በSBS አማርኛ ራዲዮ የሀገሬን ዜና በቋንቋዬ መስማቴ ከምንም በላይ ደስታ ሰጠኝ" ደራሲ ታክሎ ተሾመ
ደራሲ ታክሎ ተሾመ፤ የSBS 50ኛ ዓመት ክብረ በዓልን አስመልክተው የSBS አስተዋፅዖዎችንና ሚና በምልሰት አንስተው ግለ አተያያቸውን ያጋራሉ።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየኢትዮጵያን ድንበር የማካለል ሥራ ተቋማዊ ቅርፅ ሰጥቶ እንዲከናወን የሚያደርግ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ
በኢትዮጵያ ከሚገኙ 31 ባንኮች ውስጥ ሶስቱ ብቻ ሴት የቦርድ ሊቀመንበር እንዳላቸው ተመለከተ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"ኢትዮጵያና ሶማሊያ ታሪካዊ ጠላቶች ናቸው የሚለው በሥፍራው የሌለ ዝማሬ ነው" የቀድሞው የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር አብዲወሊ መሐመድ አሊ
የቀድሞው የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትርና የፑንትላንድ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር አብዲወሊ መሐመድ ዓሊ፤ በሶማሊያ ውስጣዊ ችግሮች፣ በሶማሊያ የኢትዮጵያ ወታደራዊ ጣልቃ ገብነትና ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች ዙሪያ የተካሔደ ውይይት (March 2017)። የSBSን 50ኛ…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየኢድ አል አድሀ በአል እርድ ተድርጎ ድሁች እንዲበሉ የሚደረግበት በአል ነው ።
ሼህ አብዱራህማን ሀጂ ከቢር በአውስትራሊይ የእስልምና እምነት ተከታዮች መሪ ፤ የኢድ አል አድሀ በአል ሀይማኖታዊ ዳራው ፤ ነብዩ ኢብራሂም ልጃቸው እስማኤልን ለመስእዋት ያቀረቡበት እና ፤ የአላህን ቃል መስማታቸውን እና መታዘዛቸውን ያስመሰከሩበት…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"ክራሬን ልቃኘውን ስጫወት መድረክ ላይ መሆኔን የማውቀው ስጨርስ ነው" ድምፃዊ ፋንታሁን ሸዋንቆጨው
ምልሰታዊ ምልከታ፤ የSBS 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል ጋር በተያያዘ ከድምፃዊ ፋንታሁን ሸዋንቆጨው ጋር የተካሔደ ቃለ ምልልስ።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛድምፃዊት ኤደን ገብረሥላሴ፤ ከሰርከስ ትግራይ እስከ ብሔራዊ መድረክ
ምልሰታዊ ምልከታ፤ የSBS 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል ጋር በተያያዘ ከድምፃዊት ኤደን ገብረሥላሴ ጋር ያካሔድነው ቃለ ምልልስ።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"SBS ለሁሉም ማኅበረሰቦች መድረክ በማቅረብ ያለውን ቁርጠኝነትና የአውስትራሊያን እውነተኛ ማንነት የሚያንፀባርቅ የሚዲያ ዐውድ እንዲቀረፅ ረድቷል"አምባሳደር አንዋር ሙክታር
አምባሳደር አንዋር ሙክታር መሐመድ በአውስትራሊያ የኢፌዴሪ ኤምባሲ ምክትል የሚሲዮን መሪ፤ የSBSን 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"የገጠመን አንዱ ተግዳሮት የሥራ አስፈፃሚው ሕገ ደንቡን መከተል አለመቻል ነው፤ ቦርዱም በቶሎ እርምት ባለመውሰዱ ትንሽ ደከም ብሏል" አቶ ተካ አዲስ
አቶ ተካ አዲስ፤ የቪክቶሪያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ፤ በሥራ አስፈፃሚ አባላት መካከል ተከስቶ ያለውን የአተያይ ልዩነት ማጥበብ እንዳልተቻለና መፍትሔ እንደሚያሻ ይናገራሉ። ግለ ምክረ ሃሳባቸውንም ያጋራሉ።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"እጁን ዘርግቶ እዚህ ላደረሰን የሜልበርንና አካባቢው ሕዝበ ክርስቲያን ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው" መልአከ ፅዮን ቀሲስ እንግዳ ቸሩ ካሣ
የሜልበርን መካነ ሰላም ቅዱስ ልደታ ለማርያም ወገብርኤል ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ፣ የሰበካ ጉባኤ አባላትና ምዕመናን የቤተክርስቲያን ግንባታ ሂደት፣ የምዕመናን ሕብረትና የአስተዋፅዖ ፋይዳዎች አንስተው ይናገራሉ።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"በSBS 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ የአድማጮቻችንና ተሣታፊዎቻችን ትልቅ አሻራ አለ፤ ላመሰግናቸው እወዳለሁ" ጋዜጠኛ ኤልያስ ጉዲሳ
የSBS አማርኛ አገልግሎት ራዲዮ ጋዜጠኛ ኤልያስ ጉዲሳ፤ የSBS 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል ጋር በተያያዘ ከጋዜጠኛነት ሙያ ጅማሮው ተነስቶ የSBS ግማሽ ክፍለ ዘመን ጉዞን ከአማርኛ አገልግሎቱ ጋር አሰናስሎ ማኅበረሰባዊና ሉላዊ አስተዋፅዖዎችን ያነሳል።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"ለSBS እና አድማጮቻችን እንኳን ለ50ኛው ዓመት አደረሳችሁ! አደረሰን! እላለሁ" ጋዜጠኛ ደመቀ ከበደ
ጋዜጠኛ ደመቀ ከበደ በኢትዮጵያ የSBS አማርኛ አገልግሎት ዋና ዘጋቢ ነው። የSBSን 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል አስመልክቶ የግል የሙያ ተሞክሮዎቹን፣ የSBS እና የSBS አማርኛ አስተዋፅዖዎችን ነቅሶ ግለ አተያዩን ያጋራል።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛአውስራሊያ እሥራኤል ላይ ማዕቀብ እንድትጥል ጉትጎታ እየተደረገ ነው
አውስትራሊያ ውስጥ የተከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች ምጣኔ ሃብት ላይ የ2 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ወጪን ማስከተላቸው ተመለከተ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛኢትዮጵያ የ12 ባለ ኮከብ ሆቴሎችን ደረጃ ነጠቀች
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 7.7 ቢሊየን ብር ተዘርፏል ቢባልም 'የዝርፊያ ሙከራ እንጂ ዘረፋ አልተካሔደብኝም' አለ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛWho are the Stolen Generations? - የተሰረቁት ትውልዶች እነማን ናቸው?
Australia has a dark chapter of history that many are still learning about. Following European settlement, Aboriginal and Torres Strait Islander children were…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"እንኳን ለ50ኛው ዓመት አደረሳችሁ! እንደ ማኅበረሰብ፤ መጪው 50ኛ ዓመት ብሩህ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው
SBS ከ1975 አንስቶ የአውስትራሊያ መድብለባሕል የማዕዘን ደንጊያና ድምፅ ማጉሊያ ሆኖ እስከ 2025 የተጓዘበትን የግማሽ ክፍለ ዘመን ጉዞውን ጁን 9 / ሰኔ 2 ያከብራል። ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛስንብት፤ አቶ ብዙአየነህ ኃይለማርያም ይፍጠር 1963 - 2025
የአቶ ብዙአየነህ ኃይለማርያም ይፍጠር ድንገተኛ ሕልፈተ ሕይወት ከቤተሰብ እስከ ማኅበረሰብ አባላት ብርቱ ሐዘንን ፈጥሯል። ሕልፈታቸውንም ተከትሎ አብሮ አደጋቸው አቶ ኬኔዲ ገብረየሱስ "ብዙአየነህ በማኅበረሰቡ ውስጥ ጥሩ ስም ነበረው። ሕልፈቱ በጣም…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛበእነ አቶ ጌታቸው ረዳ የተመሠረተው አዲሱ ክልላዊ ፓርቲ "ዲሞክራሲያዊ ስምረት ትግራይ" ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጊዜያዊ የምዝገባ ፈቃድ አገኘ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 14.5 ሚሊየን መንገደኞችን አጓጓዘ፤ 5.6 ቢሊየን ዶላር ገቢ አገኘ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛAlfred and Clinton are unlikely friends. Their friendship can teach migrant communities about reconciliation - አልፍሬድና ክሊንተን ለወዳጅነት የሚተሳሰቡ ዓይነት አልነበሩም፤ ለወዳጅነት መብቃታቸው ግና የፍልሰተኛ ማኅበረሰባትን ስለ ዕርቅ ግንዛቤ ሊያስጨብጥ ይችላል
Alfred is an Indonesian migrant, and Clinton is an Aboriginal man from Western Australia. Their friendship changed the way Alfred understood his identity as a…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛSBS ከጋዜጠኛነት ሙያዬ እንዳልርቅ ያደረገኝ ባለ ውለታዬ ነው፤ መልካም 50ኛ ዓመት SBS!
ጋዜጠኛ ማርታ ፀጋው፤ የSBS 50ኛ ዓመት ክብረ በዓልን ምክንያት በማድረግ በምልሰታዊ ምልከታና ከአድማስ ባሻገር የመጪ ጊዜያት አገልግሎት አተያይዋንና መልካም ምኞቷን አጣምራ ታወጋለች።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛበሕክምና ተቋማት በመካሔድ ላይ ያሉት የሥራ ማቆም አድማዎች ለሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ምክንያት እንዳይሆኑ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ትኩረት እንዲሰጠው ጠየቀ
የኢፌዴሪ ፖሊስ 47 የጤና ባለሙያዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያካሔደ መሆኑን አስታወቀ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"ልጄ ገዛኸኝ በመኪና አደጋ ከማለፉ በፊት 'እናቴ ይቅር በይኝ' ብሎኝ ነበር፤ ለካስ ስንብት ነው፤ በሕልፈቱ ልቤ ተሰብሯል" እናት ድንቅነሽ አሸብር
"ጌታሁን በጣም ጥሩ ሰው ነው፤ ተፈጥሮን የሚያደንቅ ነበር። ብንለያይም በሕልፈቱ በጣም አዝኛለሁ" በመኪና አደጋ ሕይወቱ ያለፈ የጌታሁን ዝግታ የቀድሞ ባለቤት ዳናዊት ሕሉፍ። የወጣት ገዛኸኝ ታደሰ ፀሎተ ፍትሐት ቅዳሜ ግንቦት 16 / ሜይ 24 በደብረ…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛኢትዮጵያ ከቻይና - ቻይና ከኢትዮጵያ የሚሹት ምንድን ነው?
በአሁኑ ወቅት በሕይወት የሌሉት የቀድሞው የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ስዮም መስፍን በሕይወት ሳሉ ከSBS አማርኛ ጋር ባካሔዱት ቃለ ምልልስ የኢትዮ - ቻይና ዲፕሎማሲያዊና ምጣኔ ሃብታዊ ግንኙነቶችንና የወደፊት…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛከማገብት እስከ ሕወሓት - አምባሳደር ስዩም መስፍን
በአሁኑ ወቅት በሕይወት የሌሉት የቀድሞው የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ስዮም መስፍን በሕይወት ሳሉ ከSBS አማርኛ ጋር ባካሔዱት ቃለ ምልልስ ከትጥቅ ትግል ጅማሯቸው ተነስተው፤ ከሕወሓት አመራር በፈቃዳቸው ስለምን…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛለኢትዮጵያውያን የውጭ ሀገራት የግል ተጓዦች የውጭ ምንዛሪ ጥሬ ገንዘብ ወደ 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ከፍ ሲል ለንግድ ሥራ መንገደኞች 15 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ተፈቅዷል
የአማራ ክልል ዳኞች በፖለቲካዊ፣ ሃይማኖታዊ ወይም አወዛጋቢ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በማናቸውም ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ሃሳብ እንዳይሰጡ የሚከለክል ደንብ ፀደቀ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"ከአክሊሉ ኃብተወልድ ወዲህ ከተማ ይፍሩ፣ ምናሴ ኃይሌና ይልማ ደሬሳ ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው ታላላቅ ዲፕሎማቶች ናቸው" አምባሳደር ዘውዴ ረታ
በ77 ዓመታቸው ከአንድ አሠርት ዓመት በፊት ከእዚህ ዓለም ከመለየታቸው በፊት የቀድሞው የኢትዮጵያ ታሪክ ተመራማሪ፣ ደራሲ፣ ጋዜጠኛና ዲፕሎማት ከነበሩት አምባሳደር ዘውዴ ረታ ጋር በሙያ ሕይወታቸው፣ የሥነ ፅሁፍ በረከቶቻቸውና ዲፕሎማሲ ዘርፍ ዙሪያ…

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"ኢሬቻ ቱሉ / አፍራሳ ኦሮሞዎች እግዚአብሔር ላደረገላቸው ምስጋና፤ ለወደፊቱ ልመና የሚቀርቡበት ነው" ኦቦ ዓለማየሁ ቁቤ
በሜልበርን የኢሬቻ ቱሉ / አፍራሳ ክብረ በዓል አስተባባሪዎች ኦቦ ዓለማየሁ ቁቤ፣ ኦቦ በንቲ ሆሉቃና አደይቱ ሚደቅሳ የክብረ በዓሉን ፋይዳዎችና የአከባበር ሂደቱን አንስተው ያስረዳሉ።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛለባንኮች የጥሬ ገንዘብ እጥረት እንደምክንያት ሲጠቀሱ የነበሩት አስገዳጅ የቦንድ ግዢና የብድር ጣሪያ ገደብ የሚደነግጉ መመሪያዎች ሊሻሩ ነው
ሰሞኑን በሀገር አቀፍ ደረጃ 'ከፊል' ያሉትን የሥራ ማቆም አድማ በማድረግ ላይ ያሉት የጤና ባለሙያዎች ያነሷቸው የደመወዝ፣ የጥቅማ ጥቅምና ምቹ የሥራ ሁኔታ ጥያቄዎቻቸው ምላሽ ካላገኙ 'ሙሉ' የሥራ ማቆም አድማ ሊያደርጉ እንደሚችሉ አሳሰቡ፤ የጤና…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"200 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የሚያወጡ የእርዳታ ቁሳቁሶችን ወደ ጂግጂጋ እየላክን ነው፤ ቀጣዩ ጎንደር ነው" ዳይሬክተር ጃማ ፋራህ
"የፉትስክሬይ ሮታሪ ክለብ፣ በጎ ፈቃደኞች፣ የአውስትራሊያ የሕክምና ተቋማትንና ለ19ኛ ዙር የተለያዩ የእርዳታ ቁሳቁሶችን ወደ ኢትዮጵያ ለመላክ የወጪ ድጋፋቸውን የቸሩ ኢትዮጵያውያን - አውስትራሊያውያን የማኅበረሰብ አባላትን በአውስትራሊያ ኢፌዴሪ…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ#86 When? Talking about time (Med) - #86 When? Talking about time (Med)
Learn how to talk about time. - Learn how to talk about time.
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛHave you been told your visa will be cancelled? This is how misinformation enables visa abuse - ቪዛዎ ሊሰረዝ እንደሚችል ተነግርዎታልን? የተሳሳተ መረጃ እንደምን ለአግባብ የለሽ የቪዛ ተፅዕኖ እንደሚዳርግ እነሆ
The migration system is complex and confusing. Experts say a lack of accessible support and credible information is leading to visa abuse. - የፍልሰት ሥርዓት ውስብስብና…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛበቀንድ ከብቶች ከአፍሪካ የአንደኛነት ሥፍራን የያዘችው ኢትዮጵያ የአንድ ዜጋ ዓመታዊ የወተት ፍጆታ 20 ሊትር ብቻ መሆኑ ተመለከተ
በኢትዮጵያ የልጅነት እርግዝና 13 በመቶ መድረስ አሳሳቢ ሆኗል
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛሱዛን ሊ የመጀመሪያዋ የሴት ሊብራል ፓርቲ መሪ ሆኑ
ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚን ጨምሮ አዲሱ የሌበር መንግሥት ካቢኔ አባላት ቃለ መሐላ ፈፀሙ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየኢትዮጵያውያን ተመራማሪዎች ጥናታዊ ፅሑፎች 'ከእውነታ የራቁ ወይም ከፍተኛ የጥራት ችግር ያለባቸው' ናቸው በሚል ከሁሉም በላቀ መልኩ እየተሰረዙ መሆኑ ተነገረ
'በሕገ ወጥ የማዕድን ቁፋሮና ዝውውር ውስጥ የክልሎችና የአካባቢ ባለስልጣናት እጆች አሉበት' አሉ የምክር ቤት አባላት
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"ሀገራችንን በእናት የምንመስላት በጣም ስለምንወዳት ነው፤ እናት የፍቅር ተምሳሌት ናት" ሜሮን ተስፋዬ
ወ/ት ሰላማዊት ወሰን ከብሪስበን "በተለይ ያለ አባት ልጆቻቸውን ላሳደጉ እናቶች 'እንኳን ለእናቶች ቀን አደርሳችሁ' ማለት እፈልጋለሁ" ሲሉ፤ ወ/ሮ ቤተልሔም ጥበቡ ከሜልበርን "እናትነትን በቃላት መግለፅ አይቻልም፤ እናትነት ትልቅ ስጦታ ነው" ይላሉ፤…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ*** በመላው አለም ለምትገኙ እናቶች በሙሉ እንኳን ለእናቶች ቀን አደረሳችሁ ***
በመላው አለም ለምትገኙ እናቶች በሙሉ እንኳን ለእናቶች ቀን አደረሳችሁ ። " እናቶችን ማክበር ማለት ሰላምን መፍጠር ለእኩልነት መቆም ማለት ነው " በሚል መርህ የተነሳቸው አሜሪካዊቷ አና ጃርቪስ ቀኑ ሲከበር ዛሬም ድረስ የእናቶች ቀን እናት በመባል…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"የዓባይ ወይስ ቬጋስ ፊልም ትኩረት ፍቅር ነው፤ ተመልካቹ የፍቅርን ታላቅነት እንዲያይና እንዲያከብር ለማስገንዘብ ነው" ዳይሬክተርና ተዋናይ ቴዎድሮስ ተሾመ
ቴዎድሮስ ተሾመ ከበደ፤ ፀሐፊ፣ ዳይሬክተርና ተዋናይ ነው። በቅርቡ ሰሞነኛ የነበረውን ዓባይ ወይስ ቬጋስ ፊልሙን 'የኢትዮጵያ ኔትፊሊክስ' ሲል በጠራው Habeshaview TV አማካይነት ለሕዝብ ዕይታ አቅርቧል። ስለ ፊልሙ ጭብጥ፣ በባሕር ማዶና ሀገር…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛንፅፅሮሽ - ኢትዮጵያና አውስትራሊያ፤ "ነፃና ፍትሐዊ ምርጫ አየሁ" የመጀመሪያ ጊዜ መራጭ ጋዜጠኛ ኤልያስ ጉዲሳ
ጋዜጠኛ ኤልያስ ጉዲሳ፤ ሀገር ቤት የጋዜጣና መፅሔት አሳታሚና ባለቤት ሆኖ ዘግቧል። በድምፅ ሰጪነትም ተሳትፏል። በኬንያ የስደት ሕይወቱም ድኅረ ምርጫ ያስከተላቸውን የሕይወት ጥፋትና የንብረት ውድመት ትኩረት ሰጥቶ ተመልክቷል። በሀገረ አውስትራሊያም…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየአውስትራሊያ ሊብራል ፓርቲ ድል የተነሳውን ፓርቲውን መልሶ ለመገንባትና የፓርላማ ወንበራቸውን ያጡትን መሪውን ለመተካት እየተጣደፈ ነው
ጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ 86 አብላጫ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወንበሮችን ይዘው የሁለተኛ ዙር አስተዳደራቸውን ጀመሩ፤ የምርጫ ድምፅ ቆጠራው ሲጠናቀቅ የሌበር ፓርቲ የምክር ቤት ወንበሮች እስከ 90 ሊደርሱ እንደሚችሉ ግምት አለ።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ የተማሪዎች ዕዳ ቅነሳ፣ የተፈጥሮ ጥበቃና የቤቶች ግንባታ የቀጣዩ መንግሥታቸው ቀዳሚ ተግባራት እንደሚሆኑ አስታወቁ
የሊብራል ፓርቲ በሌበር ፓርቲ ዕጩ ድል ተነስተው የምክር ቤት ወንበራቸውን ያጡትን የቀድሞው መሪውን የመተካት ሂደት ጀመረ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየውጭ ሀገር ዜጎች የመሬትና የንብረት ባለቤት እንዲሆኑ የሚፈቅደው ረቂቅ አዋጅ ወደ ፓርላማ ተመራ
የአውስትራሊያ ማዕድን አሳሽ አስካሪ ሜታልስ ኩባንያ በኢትዮጵያ ሥራ ጀመረ

SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛHow to vote in the federal election - ለሀገር አቀፉ ምርጫ ድምፅዎን እንደምን መስጠት እንደሚችሉ
On election day the Australian Electoral Commission anticipates one million voters to pass through their voting centres every hour. Voting is compulsory for…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"ወደፊት መራመድ አለብን፤ መተዳደሪያ ደንባችን መከለስ አለበት" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ የማኅበረሰብ አመራርና ግለ ተሞክሯቸውን አጣቅሰው ይናገራሉ።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"መሠረታችን ማኅበረሰቡ ነው፤ ወደፊት የሚያራምደን የማኅበረሰቡ ድጋፍ ነው" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አመራር አባላት "ከአንድ የሥራ ዘመን ወይም ሶስት ዓመታት በላይ ማገልገል የለባቸውም" ይላሉ። ስለምን? አተያያቸውን ያጋራሉ።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ"እኛ ፖለቲካዊ አቋም የለንም፤ የሃይማኖት አቋም የለንም፤ መሥራት ያለብን ማኅበራዊ ችግሮችን ለመቅረፍ ነው" ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው
ዶ/ር ተስፋዬ ይግዛው፤ በቪክቶሪያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ፕሬዚደንት፤ ስለ ማኅበሩ ወቅታዊ እንቅስቃሴዎች ያስረዳሉ።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛጠቅላይ ሚኒስትር አንቶኒ አልባኒዚ በቅዳሜው ሀገር አቀፍ ምርጫ ዳግም ለመመረጥ ከበቁ ከፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ታሪፍን አስመልክተው እንደሚነጋገሩ አስታወቁ
የካናዳ ተቃዋሚ ቡድን መሪ የምክር ቤት ወንበራቸውን አጡ
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛኢትዮጵያን ጨምሮ 13 ሀገራት የሩስያና ቻይና የጨረቃ ምርምር ጣቢያ ፕሮጄክትን ተቀላቀሉ
የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ቡድን 'የትግራይ ሊብራል ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ' በሚል ስያሜ አንድ የፖለቲካ ድርጅት ሊያቋቁም ነው።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየካናዳ ሊብራል ፓርቲ የፌዴራል ምርጫ አሸንፎ ዳግም ወደ መንግሥታዊ መንበረ ስልጣን ተመለሰ
የጋዛ ጦርነት ቅዳሜ ሜይ 3 በሚካሔደው የአውስትራሊያ ፌዴራል ምርጫ፤ በሁለቱ ዋነኛ ፓርቲዎች ሌበርና ሊብራል/ናሽናልስ ላይ አንዱ ዋነኛ የፖሊሲ ተፅዕኖ አሳዳሪ ጉዳይ ሆኗል።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ28 የኢትዮጵያ የንግድ ባንኮች 1.3 ቢሊየን ብር መጭበርበራቸው ተገለጠ
ለተሽከርካሪዎች ኢንዱስትሪ ራሱን የቻለ የሥርዓተ ደንብ ረቂቅ ፖሊሲ እየተዘጋጀ ነው
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛWho's Right? Who's Left? What role will religion play in this election? - ቀኝ ክንፈኛ ማን ነው? ግራ ክንፈኛ ማን ነው? በዘንድሮው ምርጫ ሃይማኖት ምን ዓይነት ሚና ይኖረዋል?
The differing and diverse religious beliefs Australians hold will influence their vote this election. - አውስትራሊያውያን ይዘዋቸው ያሉት የተለያዩና ዝንቅ ሃይማኖታዊ እምነቶች በዘንድሮው ምርጫ…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛክፍተትን ማጥበብ ማለት ምን ማለት ነው ?
አውስትራሊያ ረጅም እድሜን የሚኖሩ ሰዎች አሉባት ከሚባሉ አገራት መካከል አንደኛዋ ናት ።በአማካኝ አንድ አውስትራሊያዊ የ83ተኛ የልደት በአሉን ያከብራል። ነገር ግን የአቦርጅናል እና ቶርስት ስትሬት አይላንደር ሕዝቦች ከተቀረው አውስትራሊያውያን የእድሜ…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛለሁለት ሺህ አመት ሳይቀየር የዘለቀው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤ/ክ አምልኮ ስርአት፤ በዋሽንግተን ዲሲ ርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተ-ክርስቲያንም ቀጥሏል
ቀሲስ አብርሀም ሀብተ ስላሴ በዋሽንግተን ዲሲ ርእሰ አድባራት ደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም አገልጋይ ፤ “ ባህላችን ጥንታዊ ነው የተቀዳውም ከመጀመሪያዎቹ የክርስትና አማኞች ነው ፤ ቅዱስ በሆነ ባህል እናምናለን መጽሀፍ ቅዱስም አለን ፤ እነዚህ ሁለቱ…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየተቃዋሚው ፓርቲ በምርጫው ካሸነፈ ለመከላከያ በጀት እንደሚጨምር አስታወቀ
የፖፕ ፍራንሲስ የቀብር ስነ ስርአት በመጪው ቅዳሜ በቫቲካን ይፈጸማል ፤ ታላላቅ ሰዎች እና የአገራት መሪዎች በቀብሩ ላይ እንደሚገኙ ማረጋገጫን ሰጥተዋል ፡፡
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛየኢትዮጵያ መንግስት የፍርደኛ እስረኞች ልውውጥ የመግባቢያ ሰንድን እንዲፈርም የናይጄሪያ መንገስት ጠየቀ
የናይጄርያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ቢያንካ ኦጁኩ ፤ በአቡጃ ናይጄርያ ከኢትዮጵያ አምባሳደር ለገሰ ገረመው ጋር ሰሞኑን በተወያዩበት ወቅት ነው ጥያቄውን ያቀረቡት ፡፡
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ" አብያተ ክርስቲያናት መብዛታቸው መልካም ቢሆነም ፤ አካሄዳቸው ግን የእግዚአብሄርን መንገድ ባልለቀቀ መልኩ መሆን አለበት " - ዘማሪ ዳንኤል አምደሚካኤል
ዘማሪና ፓስተር ዳንኤል አምደሚካኤል ወደ አውስትራሊያ ለወንጌላዊ አገልግሎት በመጡበት ወቅት በክርስቲያናዊ ህይወታቸው እና አገልግሎታቸው ዙሪያ ላነሳልላቸው ጥያቄዎች ምላሻቸውን ሰጥተውናል ። በዝማሬ ህይወታቸውም ስምንት ሙሉ አልበሞችን የሰሩ ሲሆን…
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛዜና - የፖፕ ፍራንሲስን ከዚህ አለም በሞት መለየትን ተከተሎ በአውስትራሊያ ባንዲራዎች ከግማሽ በታች እንዲውለበለቡ ጠቅማይ ሚ/ር አንቶኒ አልበኒዚ አዘዙ
ፖፕ ፍራንሲስ የመጨረሻውን የፋሲካ በአል መልእክታቸውን ከቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ በረንዳ ላይ ካስተላለፉ ከአንድ ቀን በኋላ ነው ክዚህ አለም በሞት የተለዪት።
SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛበአውስትራሊያ ለቅድሚያ ምርጫ የተመዘገቡ ከነገ ጀምሮ መምረጥ ይችላሉ
18 ሚሊዮን የሚሆኑ አውስትራሊያውያን ለቅድሚይ ምርጫ የተመዘገቡ ሲሆን ፤ 60 ሚሊዮን የሚሆን የምርጫ መስጫ ወረቀቶች መታተማቸውንም የምርጫ ኮሚሽን አያይዞ አስታውቋል ፡፡